የፍትህ ሚኒስቴሩ መልዕክት

የክቡር ፍትህ ሚኒስቴሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ መልዕክት

  • ፍትህ ሚኒስቴር የሀገራችን የዴሞክራሲና ፍትህ መሰፈን፣ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲሁም የህዝቡ የላቀ ተጠቃሚነት ያለ ሕግ የበላይነትና የፍትህ ዘርፍ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ የአገራችን የፍትህ ዘርፍ ታሪክ ስር በሰደዱ አናቂ የሕግና የአሰራር እንዲሁም የአመለካካት ችግሮች የተተበተበ እና የጉልበተኞች ምርኮኛ እንደነበር ይታወሳል፡፡
  • በተጀመረው አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ተቋማችን የሕግ እና ፍትህ ሪፎርም በማከናወን እንዲሁም የአሰራር ችግሮችን በማሻሻል፣ ከሰብአዊ መብት አኳያ የሕግ ታራሚዎችን አያያዝ በማስተካከል ተቋማዊ አግልግሎትን ቀልጣፋ፣ ፍትሀዊና ውጤታማ የሆኑ የፍትህ ተደራሽነትን በማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ መሠረታዊ የለውጥ ተግባራትን አከናውኗል፣በማከናወን ላይም ይገኛል፡፡
  • ፍትህ ሚኒስቴር በአገራዊ የለውጥ ጉዞ ዳር ለማድረስ በሚደረገው ሰፊና ሁለንተናዊ ርብርብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በአዋጅ ቁጥር 943/2008 በተሰጠው ስልጣን የፍትህ እና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማክበርና ማስከበር፣ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ ፍትህን በማስፈን፣ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጡ ሀገራዊ ተልዕኮውን ከመቸውም ጊዜ በላቀ ደረጃ በመወጣት ላይ ነው፡፡
  • ተቋሙ የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማረጋገጥ የህዝብና የመንግስት አመኔታ የተቸረው ተቋም በመሆን የሀገራችንን ሰላም አስተማማኝና ዘላቂ በማድረግ የተጀመረው የልማት፣ የሰላም፣ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲጎለብት ብሎም የፍትህ ሥርዓትን ግልፅነት፣ ነፃነትና ተጠያቂነት አሰራርን በማሻሻል በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በዘላቂነት ለውጡን ለማፋጠን የነቃና የተጠናከረ የህዝብ እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ከመቸውም ጊዜ በላይ ያስፈልጋል፡፡ ፍትህ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና መሰረት ነው፡፡
  • ፍትህ የምክንያታዊነትና የእውነት ማንፀባረቂያ ሲሆን የሕግ የበላይነትን በማክበርና በማስከበር አገራችን በሁሉም መስክ የተለወጠችና የበለጸገች፣ የዴሞክራሲና የፍትህ ተምሳሌት እንድትሆን ለማድረግ በሚከናውኑ ተግባራት ላይ መላው የአገራችን ህዝብ ከጎናችን በመቆም የሕግ የበላይነትን በማስፈንና ተቋማዊ ለውጡን ለማረጋገጥ በምንሰራው ስራ በባለቤትነት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የለውጡ ፈፃሚና ዋና ተዋናኝ እንድትሆኑ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡
ራዕይ፣ተልዕኮና እሴቶች

ራዕይ፣ተልዕኮና እሴቶች

ራዕይ፣ተልዕኮና እሴቶች

ራዕይ

በ2022 የአፍሪካ የፍትሕ ተቋማት ተምሳሌት ሆኖ ማየት

ተልዕኮ

የህግ የበላይነትንና ሰብዓዊ መብትን በማክበርና በማስከበር፤ ወንጀልን በመከላከል፣ ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥና የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማስጠበቅ፤ የሕዝብ ዓመኔታ ያተረፈ ተደራሽ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት መስጠት፡፡

እሴቶች

ሰብዓዊ ክብር የሕግ የበላይነት ታማኝነት ተጠያቂነትና ግልጽነት ሙያዊ ብቃት/ፕሮፌሽናሊዝም/ ትብብርና አጋርነት ፍትሐዊነት

“ለሕግ፣ ለፍትህ፣ ለርትዕ ”

“Endangering human life for profit should be a universal crime.”

አግኙን

አግኙን

አድራሻችን

Bambis, Jomo Kenyatta Avenue,Addis Ababa, Ethiopia

ኢ_ሜይል

[email protected]

ይደውሉልን

011 551 5099